ሕክምናHikimna · Amharic health reference
በሐኪም (MD) የተጻፈ። ለትምህርት ብቻ ነው። Written by an MD. Educational only.
2

ሙቀትና በርበሬ፦ አንድ ሴንሰር

Heat and berbere: one sensor

በሐኪም (MD) የተጻፈ · Written by an MD · 2026-09-20

ምንድን ነው?

በርበሬ፣ ሚጥሚጣና ቃሪያ ውስጥ ካፕሴይሲን (capsaicin) የሚባል ኬሚካል አለ። ይህ ኬሚካል የሚሠራው በአፋችን ካሉ ነርቮች ላይ ባለ ሴንሰር (receptor) ላይ ነው። ይኸው ሴንሰር የሚያም ሙቀት ሲኖርም ይነቃል። አንዱ በሙቀት፣ ሌላው በኬሚካል፣ ሁለቱም አንድ ሴንሰር ያነቃሉ። ነርቮቹ ወደ አንጎል «እየተቃጠልኩ ነው» የሚል ሲግናል ይልካሉ። MedlinePlus፣ NIH NLM Bookshelf።

ለዚያ ነው ከፍሪጅ የወጣ ወጥም አፍ የሚያቃጥለው። ወጡ ኮልድ ነው፤ ሴንሰሩ ግን አክቲቭ ነው። የማቃጠል ስሜቱ እውነተኛ ነው፤ የአፍ ቲሹ ግን በእውነት አልተቃጠለም። ምግቡን ማቀዝቀዝ በውስጡ ያለውን ካፕሴይሲን አያስወግደውም።

ለኢትዮጵያውያን ይህ የዕለት ጉዳይ ነው። በርበሬ የባህላችን አካል ነው። ለብዙ ሰው ችግር የለውም። ግን ቃር (heartburn)፣ የጨጓራ ችግር ወይም የአፍ ቁስል ላለባቸው፣ በርበሬ ምልክቶችን ሊያባብስ ይችላል። NHS።

አደገኛ ምልክቶች

ከሚከተሉት አንዱ ካለ ወዲያውኑ እርዳታ ይፈልጉ፦

  • ምግብ ከበሉ በኋላ የመተንፈስ ችግር፣ የከንፈር፣ የምላስ ወይም የጉሮሮ ማበጥ፣ ወይም የሰውነት ሽፍታ። ይህ የምግብ አለርጂ (food allergy) ሊሆን ይችላል፤ በርበሬ አይደለም።
  • ኃይለኛ የደረት ማቃጠል ወይም ግፊት፣ ከትንፋሽ ማጠር፣ ላብ ወይም ወደ ክንድ ወይም መንጋጋ የሚሄድ ሕመም ጋር። ቃር ነው ብለው አይጠብቁ፤ የልብ ድካም (heart attack) ሊሆን ይችላል።
  • ደም ማስታወክ፣ ጥቁር ሰገራ፣ ወይም ምግብ መዋጥ መቸገር። NHS።

በአሜሪካ 911 ይደውሉ። በአዲስ አበባ የቀይ መስቀል አምቡላንስ 907 ነው። በሌላ ቦታ የአካባቢዎን የድንገተኛ እርዳታ ያነጋግሩ።

ቤት ውስጥ ምን ማድረግ?

  • አፍ ሲያቃጥል፣ ወተት የሚስማማዎት ከሆነ ከውሃ ይልቅ ወተት፣ እርጎ ወይም አይብ ሊያስታግስ ይችላል። ውሃ ብዙ አይረዳም።
  • እንጀራ ወይም ዳቦ አብረው መብላት ማቃጠሉን ሊቀንስ ይችላል።
  • በርበሬ ወይም ሚጥሚጣ ከነኩ በኋላ እጅዎን በሳሙና ይታጠቡ። ዓይንዎን፣ አፍንጫዎን ወይም አፍዎን አይንኩ። MedlinePlus።
  • ዓይን ውስጥ ከገባ፣ በንጹሕ ውሃ ብዙ ጊዜ ያጠቡ። አያሹ።
  • ቃር (heartburn) ካለብዎ፣ ትንሽ ትንሽ ይመገቡ፣ ከመተኛት ሦስት እስከ አራት ሰዓት በፊት አይብሉ፣ ራስዎን ከፍ አድርገው ይተኙ። NHS።
  • ሕመሙን ለማስታገስ ብለው በቀላሉ አይቡፕሮፌን (ibuprofen) አይውሰዱ፤ የጨጓራን ሁኔታ ሊያባብስ ይችላል።
ምልክቶች
  • አፍ፣ ምላስና ከንፈር ማቃጠል፤ ብዙውን ጊዜ በደቂቃዎች ውስጥ ይቀንሳል።
  • ላብ፣ የዓይን ውሃ ወይም የአፍንጫ ውሃ መፍሰስ።
  • ካፕሴይሲን (capsaicin) ያለበት እጅ ዓይን ወይም አፍንጫ ሲነካ፣ ኃይለኛ ማቃጠልና መቅላት።
  • በርበሬ የበዛበት ምግብ ከበሉ በኋላ ቃር (heartburn) ወይም የጨጓራ ማቃጠል።
  • ለአንዳንዶች የሆድ ቁርጠት ወይም ተቅማጥ።
ሐኪም መቼ ማየት?
  • ቃር (heartburn) ወይም የጨጓራ ማቃጠል በሳምንት ብዙ ቀን ካለ፣ ወይም የፋርማሲ መድኃኒት ካልረዳ።
  • ያለ ምክንያት ክብደት ከቀነሱ፣ በተደጋጋሚ ካስታወኩ፣ ወይም ምግብ ጉሮሮ ላይ የሚቆም ከመሰለዎ። NHS።
  • አፍዎ ያለ በርበሬም ለወራት በየቀኑ የሚያቃጥል ከሆነ። ይህ በርኒንግ ማውዝ ሲንድሮም (burning mouth syndrome) ሊሆን ይችላል፤ መጀመሪያ የጥርስ ሐኪም ያማክሩ። NIDCR።
  • የአፍ ቁስል ከሦስት ሳምንት በላይ ካልዳነ።
መከላከያ
  • ቃር ወይም የጨጓራ ችግር ካለብዎ፣ የበርበሬን መጠን ይቀንሱ፤ ምግቡን ሙሉ በሙሉ መተው ላያስፈልግ ይችላል።
  • በርበሬ ያለበትን ምግብ ባዶ ሆድ ላይ ወይም ማታ ከመተኛት በፊት አይብሉ።
  • ለልጆች የበርበሬን መጠን ትንሽ ያድርጉ፤ ሴንሰሩ ለእነሱም ይሠራል።
  • በርበሬ ከቀነጠሱ ወይም ካዘጋጁ በኋላ እጅዎን ወዲያውኑ ይታጠቡ።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
  • ቃር ያለብኝ በርበሬ ብቻ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለ?
  • የአፌ ማቃጠል ያለ ምግብም ከቀጠለ ምን መመርመር አለብኝ?
  • የምወስዳቸው መድኃኒቶች የጨጓራዬን ችግር ያባብሳሉ?
  • በርበሬን ሙሉ በሙሉ መተው አለብኝ ወይስ መቀነስ በቂ ነው?
ምንጮች

ጥያቄዎችና መልሶች · 2

alex

geographic ታንግ እንዴት ይታከማል

ሕክምና

ጂኦግራፊክ ታንግ ጉዳት የሌለው ሲሆን ብዙ ጊዜ ህክምና አያስፈልገውም፤ ምልክቱ ቦታ እየቀያየረ ይጠፋል ይመለሳል። ካቃጠለ ግን በርበሬ የበዛበት፣ ኮምጣጣና በጣም ትኩስ ምግብ መቀነስ ይረዳል።

ከቲክቶክ የመጣ ጥያቄ

እኔ ሎሚ ቃሪያ ስንጅብል በጥቅሉ መራራ ነገር በጣም ነዉ የምወደዉ መተዉ አልቻልኩም እስካሁን በጣም ደና ነኝ ጓደኞቼ ለጤና ጥሩ አደለም መሀን ያረጋል ይሉኛል ምን ላድርግ

ሕክምና

ሎሚ፣ ቃሪያና ዝንጅብል መካንነት እንደሚያመጡ የሚያሳይ ማስረጃ የለም። በልኩ ሲበሉ ለአብዛኛው ሰው ችግር የላቸውም። ለአንዳንድ ሰው ግን ቃር ወይም የጨጓራ ማቃጠል ሊያባብሱ ይችላሉ፤ እንዲህ አይነት ስሜት ከሌለዎት መተው አያስፈልግዎትም።

ጥያቄዎ ከታየ በኋላ እዚህ ይወጣል። · Your question appears after it is checked.

ተያያዥ ርዕሶች

በሐኪም (MD) የተጻፈ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን