ሕክምናHikimna · Amharic health reference
በሐኪም (MD) የተጻፈ። ለትምህርት ብቻ ነው። Written by an MD. Educational only.

ዝቅተኛ ኋይት ብለድ ሴል ቆጠራና የደፊ ነል ልዩነት

Low white blood cell count and the Duffy-null trait

በሐኪም (MD) የተጻፈ · Written by an MD · 2026-09-20

ምንድን ነው?

ኋይት ብለድ ሴል (white blood cell) ሰውነትዎ ኢንፌክሽንን የሚከላከልባቸው የደም ሴሎች ናቸው። ኒውትሮፊል (neutrophil) ከእነዚህ አንዱ ዓይነት ነው። በላብ ሪፖርት ላይ ኤ ኤን ሲ (ANC) የሚባለው ቁጥር በደም ውስጥ ያሉትን ኒውትሮፊሎች ይቆጥራል። ይህ የጠቅላላ ኢሚዩኒቲ (immunity) ስኮር አይደለም። የላብ «ኖርማል» ክልል ከላብ ወደ ላብ ትንሽ ይለያያል፤ ዕድሜ፣ ጾታና ዘር ሊነኩት ይችላሉ። MedlinePlus፣ NIH NHLBI።

ደፊ ነል (Duffy-null) የሚባል ከቤተሰብ የሚወረስ የብለድ ግሩፕ ልዩነት አለ። እሱ ያላቸው አንዳንድ ጤነኛ ሰዎች ኤ ኤን ሲ በተፈጥሮ ዝቅ ያለ ነው። ይህ ልዩነት በራሱ የኢንፌክሽን ሪስክ አይጨምርም። ቀድሞ «ቤናይን ኤትኒክ ኒውትሮፒኒያ» (benign ethnic neutropenia) ይባል ነበር፤ አሁን ደፊ ነል አሶሺዬትድ ኒውትሮፊል ካውንት (Duffy-null associated neutrophil count) ይባላል። በአፍሪካ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ዘንድ የተለመደ ነው፤ ግን በሌሎችም ይገኛል። ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻ ደፊ ነል አለዎት ማለት አይደለም። ASH።

ለዲያስፖራ አስፈላጊው ነጥብ ይህ ነው፦ «ሎው» ስላለ መደናገጥም፣ «ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ኖርማል ነው» ብሎ መተውም ትክክል አይደለም። ዝቅተኛ ኋይት ብለድ ሴል ከመድኃኒት፣ ከቫይረስ ኢንፌክሽን፣ ከኦቶኢሚዩን (autoimmune) በሽታ ወይም ከቦን ማሮው (bone marrow) ችግርም ሊመጣ ይችላል። አንድ ሪዛልት ብቻ ሙሉ ታሪኩን አይነግርም። MedlinePlus።

አደገኛ ምልክቶች

ከሚከተሉት አንዱ ካለ ወዲያውኑ እርዳታ ይፈልጉ፦

  • ዝቅተኛ ኒውትሮፊል (neutrophil) እንዳለዎት እያወቁ ትኩሳት ካመጡ፤ በተለይ ቁጥሩ በጣም ዝቅተኛ ከሆነ፣ ወይም ኬሞቴራፒ (chemotherapy) እየወሰዱ ከሆነ። ትኩሳት 38 °C (100.5 °F) ወይም ከዚያ በላይ ኢመርጀንሲ ሊሆን ይችላል። NCI።
  • ብርድ ብርድ ማለትና ላብ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ከባድ ድካም ወይም ግራ መጋባት።
  • ትኩሳትን ለመሸፈን መድኃኒት ወስደው አይጠብቁ፤ በአሜሪካ 911 ይደውሉ ወይም ወደ ኢመርጀንሲ ይሂዱ። በአዲስ አበባ የቀይ መስቀል አምቡላንስ 907 ነው፤ በሌላ ቦታ የአካባቢዎን የድንገተኛ እርዳታ ያነጋግሩ።

ቤት ውስጥ ምን ማድረግ?

  • ከኢትዮጵያም ሆነ እዚህ ያለዎትን የቀድሞ ሲ ቢ ሲ (CBC) ሪከርድ ይያዙ። ቁጥሩ ከበፊትም እንዲህ ነበር? ይህ ለሐኪምዎ ትልቅ መረጃ ነው።
  • የሚወስዷቸውን መድኃኒቶች፣ የቅርብ ጊዜ ኢንፌክሽኖችንና የቤተሰብ ታሪክዎን ይመዝግቡ።
  • መድኃኒትዎን በራስዎ አያቁሙ። አንዳንድ መድኃኒቶች ኋይት ብለድ ሴል ሊቀንሱ ይችላሉ፤ ግን ውሳኔው ከሐኪምዎ ጋር ነው።
  • ቁጥርዎ በእውነት ዝቅተኛ ከሆነ፣ እጅዎን በተደጋጋሚ ይታጠቡ፣ ከታመሙ ሰዎች ይራቁ፣ ስጋ፣ ዓሳና እንቁላል በደንብ የበሰሉ ይሁኑ። NCI።
  • «ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ኖርማል ነው» ብለው ብቻዎን አይወስኑ፤ ደፊ ነል (Duffy-null) በምርመራ ይረጋገጣል።
ምልክቶች
  • ደፊ ነል (Duffy-null) ያላቸው ጤነኛ ሰዎች ብዙ ጊዜ ምንም ምልክት የላቸውም፤ ቁጥሩ የሚታወቀው በሲ ቢ ሲ (CBC) ምርመራ ብቻ ነው።
  • ቁጥሩ ከበፊት ሪከርድዎ ጋር ተመሳሳይ ከሆነ፣ ሌሎቹ የደም ሴሎች ኖርማል ከሆኑና ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን ከሌለ፣ ይህ የሚያረጋጋ ምልክት ነው።
  • በሌላ ምክንያት የመጣ ዝቅተኛ ኒውትሮፊል (neutrophil) ግን ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን፣ ትኩሳት፣ የጉሮሮ ሕመም ወይም የአፍ ቁስል ሊያመጣ ይችላል።
ሐኪም መቼ ማየት?
  • ሪፖርትዎ ላይ «ሎው» ሲጻፍ በቀጣዩ አፖይንትመንት ይወያዩ። አንድ ሪዛልት ብቻውን ዲያግኖሲስ አይደለም።
  • አዲስ መቀነስ (ከቀድሞ ሪከርድዎ ያነሰ)፣ በጣም ዝቅተኛ ቁጥር፣ ወይም ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን ካለ የዶክተር ግምገማ ያስፈልጋል።
  • ሌሎቹ የደም ሴሎችም (ቀይ የደም ሴል፣ ፕሌትሌት (platelet)) ዝቅ ካሉ፣ ተጨማሪ ምርመራ ሊያስፈልግ ይችላል። NIH NHLBI።
  • ደፊ ቴስት (Duffy test) ለእርስዎ ያስፈልግ እንደሆነ ይጠይቁ። ደፊ ነል መሆንዎ ከተረጋገጠ፣ በሜዲካል ሪከርድዎ እንዲጻፍ ይጠይቁ። ይህ ለወደፊት የመድኃኒት፣ የኬሞቴራፒና የክሊኒካል ትራያል (clinical trial) ውሳኔ ይረዳል፤ ያለአግባብ «ኒውትሮፒኒያ» (neutropenia) ተብለው ከመሰየም ይጠብቅዎታል። ASH።
መከላከያ
  • ደፊ ነል (Duffy-null) የሚወረስ ልዩነት ነው፤ አይከላከልም፣ አያስፈልግምም። የሚከላከሉት የተሳሳተ ዲያግኖሲስንና ያልተፈለገ ምርመራን ነው።
  • የሲ ቢ ሲ (CBC) ውጤቶችዎን በአንድ ቦታ ያስቀምጡ፤ ሐኪም ሲቀይሩ ወይም አገር ሲቀይሩ ይዘው ይሂዱ።
  • ደፊ ነል መሆንዎ ከተመዘገበ፣ ለእያንዳንዱ አዲስ ሐኪም ይንገሩ።
  • ቁጥርዎ በእውነት ዝቅተኛ ከሆነ፣ የኢንፌክሽን መከላከያ ልማዶችን ይጠብቁ፣ የታዘዙ ክትባቶችን ስለመውሰድ ሐኪምዎን ይጠይቁ።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
  • የእኔ ኤ ኤን ሲ (ANC) ለእኔ ምን ማለት ነው? ከቀድሞ ሪከርዴ ጋር ሲነጻጸርስ?
  • ደፊ ቴስት (Duffy test) ለእኔ ያስፈልጋል? ውጤቱ በሜዲካል ሪከርዴ ይጻፍልኝ?
  • መድኃኒቶቼ ወይም የቅርብ ኢንፌክሽን በቁጥሩ ላይ ተጽእኖ አላቸው?
  • ትኩሳት ካመጣሁ ወዴት ልደውል? ምን ያህል ትኩሳት ኢመርጀንሲ ነው?
ምንጮች
  • MedlinePlus. WBC count.
  • NIH NHLBI. Blood Tests.
  • American Society of Hematology (ASH). Duffy-null Associated Neutrophil Count (DANC).
  • NCI. Infection and Neutropenia during Cancer Treatment.

ጥያቄዎችና መልሶች

የመጀመሪያውን ጥያቄ ይጠይቁ።

ጥያቄዎ ከታየ በኋላ እዚህ ይወጣል። · Your question appears after it is checked.

ተያያዥ ርዕሶች

በሐኪም (MD) የተጻፈ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን